የGmail ፕሮግራም መመሪያዎች

የGmail ፕሮግራም መመሪያዎች ለሁሉም የGmail ተጠቃሚዎች አዎንታዊ ተሞክሮ በማስጠበቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህ መመሪያዎች ሊለወጡ ስለሚችሉ በየጊዜው ተመልሰው ማየትዎን እርግጠኛ ይሁኑ። እባክዎ ለተጨማሪ መረጃ የGoogle የአገልግሎት ውልን እንደማጣቀሻ በተጨማሪ ይመልከቱ።

አይፈለጌ መልዕክት እና የጅምላ መልዕክት

Gmailን አይፈለጌ መልዕክት ወይም የማይታወቅ የንግድ መልዕክት ለማሰራጨት አይጠቀሙ።

የCAN-SPAM Actን ወይም ሌሎች ፀረ-አይፈለጌ መልዕክት ህጎችን የሚጥሱ ኢሜይሎችን ለመላክ፤ በክፍት፣ ሶስተኛ ወገን አገልጋዮች በኩል ያልተፈቀደ ኢሜይል ለመላክ፤ ወይም ያለስምምነታቸው የማንኛውንም ሰው የኢሜይል አድራሻዎችን ለማሰራጨት Gmailን መጠቀም አይፈቀድልዎትም።

ተጠቃሚዎችን በሚያሳስት ወይም በሚያታልል መልኩ፣ ኢሜይሎችን ለመላክ፣ ለመሰረዝ ወይም ለማጣራትም ቢሆን፣ የGmail በይነገጽን ራስ ሰር ማድረግ አይፈቀድልዎትም።

እባክዎ «ያልተጠየቀ» ወይም «የማይፈለግ» መልዕክት ላይ የእርስዎ ትርጉም እና የኢሜይል ተቀባዮችዎ ግንዛቤ የተለየ ሊሆን እንደሚችል ልብ ይበሉ። ተቀባዮቹ ባለፉት ጊዜያት ኢሜይሎችን ከእርስዎ ለመቀበል ተመራጭ ቢሆኑም እንኳን በርካታ ቁጥር ላላቸው ተቀባዮች ኢሜይል በሚልኩበት ጊዜ የራስዎን ውሳኔ ይውሰዱ። የGmail ተጠቃሚዎች ኢሜይሎችን እንደ አይፈለጌ መልዕክት ምልክት ሲያደርጉ ወደፊት የሚልኳቸውንም መልዕክቶች በእኛ ፀረ-አላግባብ መጠቀም ስርዓቶች እንደ አይፈለጌ መልዕክት የመመደባቸውን እድል ይጨምራል።

የበርካታ የGmail መለያዎች አፈጣጠር እና አጠቃቀም

የGoogle መመሪያዎችን አላግባብ ለመጠቀም፣ የGmail መለያ ገደቦችን አላግባብ ለማለፍ፣ ማጣሪያዎችን በዘዴ ለማለፍ ወይም በሌላ መልኩ በመለያዎ ላይ የተቀመጡ ገደቦችን ለመገልበጥ በርካታ መለያዎችን አይፍጠሩ ወይም አይጠቀሙ። (ለምሳሌ፦ በሌላ ተጠቃሚ ታግደው ከነበረ ወይም በአላግባብ መጠቀም ምክንያት የGmail መለያዎ ተወግዶ ከነበረ በተመሳሳይ እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፍ ምትክ መለያ አይፍጠሩ።)

እንዲሁም የGmail መለያዎችን በራስ ሰር መንገዶች መፍጠር ወይም የGmail መለያዎችን ከሌሎች መግዛት፣ መሸጥ መነገድ ወይም ዳግም መሸጥ አልተፈቀደለዎትም።

ተንኮል አዘል ዌር

Gmailን ቫይረሶችን፣ ተንኮል አዘል ዌርን፣ ዎርሞችን፣ ግድፈቶችን፣ ተንኮል አዘሎችን፣ የተበላሹ ፋይሎችን፣ ወይም ማንኛቸውም እነዚህን የመሰሉ የማውደም ወይም የማሳሳት ተፈጥሮ ያላቸውን ለማስተላለፍ አይጠቀሙ። በተጨማሪም፣ በአውታረ መረቦች፣ አገልጋዮች ወይም የGoogle ወይም የሌሎች የሆነ ሌላ መሠረተ ልማትን ክወና የሚጎዳ ወይም በስራቸው ጣልቃ የሚገባ ይዘት አያሰራጩ።

ማጭበርበር፣ ማስገር እና ሌሎች አታላይ ልማዶች

የሌላ ተጠቃሚን የGmail መለያ ግልጽ የሆነ ፈቃዳቸው ሳይኖር መድረስ ላይችሉ ይችላሉ። ለማታለል፣ ለማሳሳት፣ ወይም ሌሎች ተጠቃሚዎችን በሐሰት ቀርበው መረጃ በመጋራት ለማታለል Gmailን አይጠቀሙ።

እንደ መግቢያ መረጃ፣ የይለፍ ቃሎች፣ የፋይናንስ ዝርዝሮች ወይም የመንግስት መታወቂያ ቁጥሮች ያሉትን የተጠቃሚዎች ውሂብ ለማስገር ወይም ሌሎችን ለማጭበርበር አንድ ዘዴ አካል ሆኖ Gmailን አይጠቀሙ።

የህጻናት ደህንነት

Google የህፃናት ወሲባዊ ጥቃት ምስሎችን የሚቃወም በፍፁም የማያወላዳ መመሪያ አለው። እንደዚህ ያለ ይዘት እንዳለ ካወቅን ህግ በሚጠይቀው መሰረት የጠፉ እና ጥቃት የደረሰባቸው ህጻናት ብሔራዊ ማዕከል ሪፖርት እናደርጋለን። እንዲሁም በጉዳዩ የተሳተፉ ሰዎችን የGmail መለያዎች ማቋረጥን ጨምሮ የቅጣት እርምጃ ልንወስድ እንችላለን።

የቅጂ መብት

የቅጂ መብት ህጎችን ያክብሩ። እውቅና፣ የንግድ ምልክት፣ የንግድ ሚስጥር ወይም ሌሎች የባለቤትነት መብቶችን ጨምሮ የሌሎች ሰዎችን የአእምሮ ንብረት መብቶች አይጣሱ። እንዲሁም የአዕምሮ ንብረት መብቶችን ሌሎች እንዲጥሱ ለማበረታታት ወይም ለማሳሳት አይፈቀድልዎትም። የቅጂ መብት ጥሰቶችን ይህን ቅጽ በመጠቀም ለGoogle ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

ትንኮሳ

Gmailን ለመተንኮስ፣ ለማስፈራራት ወይም ሌሎች ላይ ስጋት ለመፍጠር አይጠቀሙ። Gmailን ለእነዚህ አላማዎች ሲጠቀም የተገኘ ማንኛውም ሰው መለያው ሊወገድ ይችላል።

ህገወጥ እንቅስቃሴ

ህጋዊ ይሁኑ። Gmailን ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለማስተዋወቅ፣ ለማደራጀት ወይም ለመሳተፍ አይጠቀሙ።